Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተለያዩ ውሳኔዎች አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ተሰርዞ የነበረው የ13 የአፍሪካ ሀገራት የሊዝ ውል እንዲመለስ መወሰኑን የከተማው ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ ካቢኔው ከወሰናቸው ጉዳዮች መካከል የ13 የአፍሪካ ሀገራት የሊዝ ውል እንዲመለስ መድረጉ ተጠቃሽ መሆኑን ጠቁመው÷ ይህም ኤምባሲዎቹ ዳግም ወደ ስራ መግባት እንደሚያስችላቸው አስረድተዋል፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ ካቢኔው ከወሰናቸው ጉዳዮች መካከል የ13 የአፍሪካ ሀገራት የሊዝ ውል መሰረዙን ጠቁመው÷ ይህም ኤንባሲዎቹ ዳግም ወደ ስራ መግባት እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ ለቻይና የባሕል ማዕከል ግንባታ የቀረበውን ጥያቄ የከተማዋ ካቢኔ ማፅደቁን ገልጸው÷ ለዚህም 6 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ እንዲሰጥ ተወስኗል ብለዋል፡፡

ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚኖረውን የባህል፣ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚጠናክረው ነው ተናገሩት፡፡

በተያያዘ በቻይና መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የሚገነባው የአፍሪካ የቀርከሃ ሰርቶ ማሳያ ማዕከል ግንባታ ጥያቄም ምላሽ አግኝተል ብለዋል ኃላፊው።

በሌላ በኩል 35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በሰላም እንዲጠናቀቅ ጉልህ ድርሻውን ለተወጣው ሰላም- ወዳዱ ህዝብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምስጋና ያቀርባል ብለዋል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው፡፡

በሃይማኖት ኢያሱ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.