በባሌ ብሔራዊ ፓርክ አካባቢ ተነስቶ የነበረው እሳት በቁጥጥር ስር ዋለ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሌ ብሔራዊ ፓርክ አጎራባች ወረዳዎች ላይ ተነስቶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።
የዝሆኖች ሕገ ወጥ አደንና ግድያ በአንጻራዊነት መሻሻል ማሳየቱንም አመልክቷል።
የባለስልጣኑ የዱር እንስሳት ሕግ ማስከበር ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል አሰፋ እንደገለጹት፥ በአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ በተደጋጋሚ የእሳት ቃጠሎ ይነሳል፣ ተነስቶ የነበረውም በቁጥጥር ስር ውሏል።
በባሌ ብሔራዊ ፓርክ ከአራት ቀን በፊት የተነሳው እሳት ቃጠሎ በፓርኩ ውስጥ ሳይሆን በአጎራባች ወረዳዎች ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፥ በጎባና በበርበሬ መካከል በምትገኘው በስመና ኦዶ ቡሉ በምትባል ቦታ የተነሳው እሳትም ከትናንት ወዲያ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።
ወቅቱ ደረቃማ በመሆኑና የታችኛው ቆላማ አካባቢ ነዋሪዎች ወደ ደኑ አካባቢ በመምጣታቸው የእሳቱ መነሻ ከማር ቆረጣ ጋር ተያይዞ ሊከሰት እንደሚችል አመልክተው፥ እስካሁን የእሳቱ መነሻ ምን እንደሆነ እየተጣራ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።
አካባቢው ላይ ያሉ ሰዎች እሳቱን የመቆጣጠር ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራቸው አመልክተው፥ የእሳቱን መነሻ በመለየትና በማጣራት ሥራን በትኩረት እየተሳተፉ እንደሆነም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!