Fana: At a Speed of Life!

የኮሚሽነሮች የምርጫ ሂደት አሳታፊ፣ ግልጽ እና ተአማኒነት ያለው ነው – አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮችን የምርጫ ሂደት አሳታፊ፣ ግልጽ፣ ተአማኒነት ያለውና ገለልተኝነቱን ያረጋገጠ ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ያደረገ ሲሆን ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የቀረቡ 11 እጩዎችን ሹመት ዛሬ አጽድቋል።
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የኮሚሽነሮችን ምርጫ ለማካሄድ የነበረው ሂደት አሳታፊ፣ ግልጽ፣ ተአማኒነት ያለውና ገለልተኝነቱን ያረጋገጠ እንዲሆን ተደርጎ መከናወኑን ገልጸዋል።
የምክር ቤት አባላት የቀረቡት እጩ ኮሚሽነሮች አገራዊ ምክክሩን በማስተባበር የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ብቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያን በቀጣይ በሚደረገው አገራዊ ውይይት በሙያ፣ በሽምግልና፣ በልምድ አስተዋጽኦ በማድረግ በንቃት፣ በአስተዋይነት እንዲነጋገሩ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
“ይህንን ማድረግ ከተቻለ ለቀጣይ አገራችን በትክክለኛ መሰረት ላይ ልናስቀምጥ እንችላለን” በማለት ኮሚሽነሮቹ ይህን ታሳቢ ያደረገ የማስተባበር ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል ብለዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ክትትል በማድረግ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም ለምክክሩ ውጤታማነት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ምክር ቤቱ አገራዊ ምክክሩን ለመምራት የቀረቡ 11 እጩ ኮሚሽነሮችን የትምህርትና የሰራ ልምድ እንዲሁም የተቀመጡ መስፈርቶች ላይ ከተወያየ በኋላ በአምስት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ሹመቱን ያጸደቀ ሲሆን ተሿሚዎችም ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.