ሩሲያ ከ70 የሚበልጡ የዩክሬን ወታደራዊ ተቋማትን ማውደሟን ገለፀች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ከ70 የሚበልጡ የዩክሬን ወታደራዊ ተቋማትን ማውደሟን ገለፀች።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢጎር ኮናሼንኮቭ በሰጡት መግለጫ፥ ሞስኮ 11 የዓየር ሀይል ማዘዣዎችን ጨምሮ ከ70 የሚበልጡ በዩክሬን የሚገኙ ወታደራዊ ኢላማዎችን ማውደሟን አስታውቀዋል።
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን በመገንጠል ራሷን ነፃ አገር አድርጋ
ይህንን ተከትሎ በእስካሁኑ ወታደራዊ ዘመቻ በ74 የዩክሬን ወታደራዊ ተቋማት ላይ የሩሲያ ዓየር ኃይል በፈፀመው ጥቃት መውደማቸውን ኢጎር ኮናሼንኮቭ አስታውቀዋል።
ከእነዚህ ውስጥም 11 የዓየር ኃይል ማዘዣዎች፣ 18 የዓየር መቃወሚያ የተተከለባቸው የራዳር ጣቢያዎች እና ሶስት የወታደራዊ ኮማንድ ፖስት ማዕከላት እንደሚገኙበት ነው ያመለከቱት።
እንደ ቲ አር ቲ ዘገባ በኪየቭ አቅራቢያ የሚገኝ የዓየር ሀይል ማዘዣን ለመቆጣጠር የሁለቱ ሀገራት ወታደሮች ውጊያ በማድረግ ላይ ናቸው።
ዩክሬን በፊናዋ በኪየቭ አቅራቢያ ሲበር የነበረ አንድ የሩሲያን ሄሊኮፕተር እንዲሁም አምስት አውሮፕላኖችን መትቼ ጥያለሁ ብላለች።
ሞስኮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር መሰረት እና የዶኔትስክ እና የሉጋንስክ ሪፐብሊኮች ከሩሲያ ጋር በገቡት የወዳጅነት ስምምነት መሰረት እየተፈፀመ መሆኑንም ነው ያስታወቀችው።
አያይዘውም ዩክሬንን ፀረ- ሩሲያ ከሆኑ ናዚዎች ማፅዳትንም የወታደራዊ ዘመቻው ዓላማ እንደሆነ አመልክታለች።