በደቡብ ዕዝ የ30ኛ ነበልባል ክፍለ ጦር የሜዳሊያና የማዕረግ አሰጣጥ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ዕዝ የ30ኛ ነበልባል ክፍለ ጦር የሜዳሊያና በስራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላመጡ የሰራዊት አባላት የማዕረግ አሰጣጥ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ሰለሞን ኢተፋ፣ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል መሃመድ ተሰማ እና ሌሎች ጄነራል መኮንኖች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የ30ኛ ነበልባል ክፍለ ጦር ወራሪውን የህውሓት ሀይል ለመደምሰስ በተካሄደው የህልውና ዘመቻ ላይ ከፍተኛ ጀብዱ ከፈፀሙ ክፍሎች አንዱ መሆኑን ከመከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ