Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ እና ምስራቅ ሀረርጌ ወረዳዎች ከፍተኛ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ተከስቷል- የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ሀሰሊሶ እና ሁላል እንዲሁም በምስራቅ ሀረርጌ ወረዳዎች በውሃ ጉድጓዶች መድረቅና በኃይል መቆራረጥ ምክንያት ከፍተኛ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር መከሰቱን የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ገለጸ፡፡
ማህበረሰቡ በቀን 23 ሺህ ሜትር ኩብ ውሀ እንደሚያስፈልገው የተጠቀሰ ሲሆን÷ እየተዳረሰ ያለው 5 ሺህ ሦስት መቶ ሜትር ኩብ መሆኑን የክልሉ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የምህንድስና ክፍል ሀላፊ አህመድ መሀመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ በድሬዳዋም 70 ሺህ ሜትር ኩብ ውሃ በቀን እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ሲሆን÷ እየቀረበ ያለው 33 ሺህ ሜትር ኩብ ብቻ መሆኑን የ የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ መሀመድ ሙሳ ገልዋል፡፡
ከጉርጓዶች መድረቅ በተጨማሪ የካልሺየም ካርቦኔት የውሀ ቱቦዎችን መድፈን ለተጨማሪ ወጪ መዳረጉንም ተናግረዋል፡፡
የድሬዳዋ እና የሀረሪ ክልልን እድገት የሚመጥን የውሀ አቅርቦት ለማዳረስ የፌደራል መንግስት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
የምስራቁን ክፍል የውሃ ችግር ለመፍታት የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን የጎበኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ÷ ከጭሮ ጀምሮ ያለው አካባቢ በርካታ ማህበረሰብ የሚገኝበት እንደመሆኑ ከአሁን ጀምሮ ዘላቂ መፍትሄውን ማሰብ እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት፡፡
የከርሰምድርን ውሃ መንከባከብም አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በአጭር ጊዜ ተጨማሪ ጉጓዶችን ቆፍሮ ወደ ስራ ማስገባት እንደ መፍትሔ የሚቀመጥ መሆኑም ጠቅሰው÷ የአመራሩ በጋራ መንቀሳቀስ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ከፍ እንደሚያደርገውም ነው የገለጹት፡፡
በፈቲያ አብደላ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.