በአፋር ክልል በአሸባሪው ቡድን ለተፈናቀሉ ወገኖች የ100 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በአፋር ክልል አሸባሪው ህወሓት በፈጸመው ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች የ100 ሚሊየን ብር የገንዘብና ለተጎዱ ተቋማት ደግሞ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።
ከገንዘቡ ሌላ ከተደረጉት ቁሳቁሶች መካከል “ፒክ አፕ ” እና የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ኮምፒውተሮችና ሌሎችም የቢሮ መገልገያዎች ይገኙበታል።
ድጋፉን የከተማ ልማትና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ማስረከባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!