Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃትና ዲሲፕሊን መፈፀሙ የሚጠበቅና የሚያኮራ ተግባር ነው- ሜ/ጄ ቤንጃሚን አልፈሚ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በዚህ አስቸጋሪ የግዳጅ ቀጣና ውስጥ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃትና በተሟላ ወታደራዊ ዲሲፕሊን መፈፀሙ የሚጠበቅና የሚያኮራ ተግባር ነው ሲሉ በአብዬ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ጦር (የዩኒስፋ) የበላይ ጠባቂና ኃይል አዛዥ ሜ/ጄ ቤንጃሚን አልፈሚ ተናገሩ፡፡
ሜ/ጄ ቤንጃሚን አልፈሚ ሳውየር እና የዩኒስፋ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ÷ ወቅት የሻለቃው የግዳጅ ቀጣና የኃይል አሰፋፈር፣ የግዳጅ አፈፃፀምና የተገኘ ውጤት አስመልክቶ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሠላም ማስከበር ተልዕኮ የረዥም ጊዜ ልምድና ተሞክሮ ያለውና በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ግዳጁን በብቃት እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ሜ/ጄ ቤንጃሚን እንደገለጹት፥ ሻለቃው ላለፉት 19 ወራት በተሰማራበት የግዳጅ ቀጣና የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ የሰው ሕይወትንና ንብረትን መታደግ በመቻሉ ዩኒስፋ በቀጣናው ማሳካት የፈለገውን ግብ እንዲያሳካ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል ፡፡
ይህንን ልምድና ተሞክሮ ለተተኪው ሻለቃ እንደምታካፍሉም እምነቴ ነው ማታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.