Fana: At a Speed of Life!

ውድመት የደረሰባቸውን የባህልና የስፖርት ተቋማት መልሶ ሥራ ለማስጀመር ማገገሚያ እቅድ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸውን የባህልና የስፖርት ተቋማት ለማቋቋምና መልሶ ሥራ ለማስጀመር እንዲቻል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማገገሚያ እቅድ አዘጋጀ፡፡

አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን በወረራ ይዟቸው በነበሩ የአማራ እና አፋር ክልል አካባቢዎች ካደረሰው ሰብዓዊ ጉዳት በተጨማሪ ሕዝብ የሚገለገልባቸውን የባህልና የስፖርት ተቋማት እና ሌሎች ማኅበራዊ ተቋማት አውድሟል፡፡

በህዝብ እና በመንግስት የተቋቋሙ የስፖርትና የባህል ተቋማት መገልገያ እና ግብዓቶችንም ዘርፏል፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ በባህል ዘርፍ ከነበሩ ተቋማት እና አገልግሎቶች 120 ሚሊየን 824 ሺህ 930 ብር የሚገመት እና በስፖርት ዘርፍ ከነበሩ ተቋማት እና አገልግሎቶች 339 ሚሊየን 883 ሺህ 579 ብር በላይ የሚገመት ጉዳት መድረሱን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያቋቋመው ቴክኒክ ኮሚቴ ገልጿል።

በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እንዳሉት ፥ በባህልና ስፖርት ዘርፍ የህብረተሰቡን ተስፋ የሚያለመልም የስነ- ልቦና ስራ በዓይነት፣ በቁሳቁስና በስነ ልቦና ህክምና ላይ መሥራት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደሚጠበቅ በአጽንዖት ገልጸዋል።

የመልሶ ማቋቋም ስራውን የሚያስተባብር ግብረ ሃይል ተቋቁሞ በአስቸኳይ ወደ ስራ ተገብቶ ስራዎችን እያቀናጁ መስራት ያስፈልጋል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.