Fana: At a Speed of Life!

በቤት ውስጥ የዓለም ሻምፒዮን በ1 ሺህ 500 ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍፃሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በሰርቢያ እየተካሄደ ባለው 1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ፍፃሜ ማለፍ ችለዋል፡፡
በ1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ ላይ የተሳተፉት አክሱማዊት አምባዬ፣ ሒሩት መሸሻና ጉዳፍ ፀጋይ ውድድራቸውን በአንደኝነት አጠናቀው ወደ ፍፃሜው አልፈዋል።
በተመሳሳይ በወንዶች የ 3ሺህ ሜትር ማጣሪያ ውድድር ለሚቻ ግርማ እና ሰለሞን ባረጋ ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ ለፍጻሜ ደርሰዋል፡፡
በሌላ በኩል በሪሁ አረጋዊ በ3ሺህ ሜት ምድቡን 6ኛ ሆኖ በማጠናቀቁ ለፍጻሜ ማለፍ አልቻለም፡፡
የሁለቱም ፆታ የፍፃሜ ውድድር ምሽት 4 ሰዓት ከ 25 የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.