Fana: At a Speed of Life!

ወደ ቻይና ከሚላኩ የወጪ ምርቶች ጋር በተያየዘ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 9፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ወደ ቻይና ከሚላኩ የወጪ ምርቶች ጋር በተያያዘ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ የበይነ-መረብ ውይይት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ተካሂዷል።

በውይይቱ አዲሱ ህግ ድንጋጌዎችና በላኪ ድርጅቶች ላይ እየፈጠረ ያለው ተፅዕኖ በስፋት የተነሳ ሲሆን፥ ችግሩንም ለመቅረፍ በጊዜያዊነትና በዘለቄታዊነት ይረዳሉ የተባሉ የመፍትሄ ሀሳቦችም ቀርበዋል።

በውይይቱ በቻይና የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር አቶ ተሾመ ቶጋ፥ ችግሩን በጊዜያዊነት ለመቅረፍ ከቻይና ጉሙሩክ አስተዳደር ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶች እንደሚደረጉ አሳውቀው ሀገሪቱ ህጉን ያወጣችው ለሁሉም ሀገራት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ላኪዎች ያንን የሚመጥን ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው ጠቅሰዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛ ምስራቅ ፣ ኤዥያ እና ፓስፊክ አገራት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ዶ/ር ገበየሁ ጋንጋ ÷ የተፈጠረው ችግር ሀገርን ጥቅም ከማሳጣቱ ባሻገር በቻይና ገበያ ላይ ያለን ምቹ የገበያ ሁኔታ ኢትዮጵያ በአግባቡ እንዳትጠቀም የሚያደርግ በመሆኑ ባለድርሻ አካላትን ሁሉ ባካተተ መልኩ የመፍትሄ ስራዎች መሰራት አለባቸው ብለዋል።

ላኪ ድርጅቶችም እራሳቸውን የመፍትሄው አካል በማድረግና ጠንካራ ህብረት በመፍጠር የቻይና ጉሙሩክ አስተዳደር ያወጣውን መስፈርቶች ማሟላት የሚያስችል አቅም መፍጠር እንዳለባቸው መግለፃችን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.