በኢትዮጵያ ፀጥታና ደህንነት ዘርፍ የተካሄደውን የሪፎርም ስራ የሚዳስስ መጽሐፍ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የፀጥታና የደህንነት ዘርፍ ላይ የተካሄደውን የሪፎርም ስራ ጨምሮ አጠቃላይ ሃገራዊ የለውጥ ስራዎችን የሚዳስስ መጽሐፍ ተመረቀ።
መጽሐፉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎትና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በጋራ ያዘጋጁት መሆኑ ተገልጿል።
መጽሐፉ በሶስት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞና እንግሊዝኛ ነው የተዘጋጀው ።
በቀጣይም በሌሎች ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ ለፌደራልና ለክልል የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ባለሙያዎች ግብዓት እንዲሆን በየክልሉ እንደሚሰራጭ መገለጹን ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!