በጎንደር ከተማ በህዝብ እና በህዝብ ተመራጮች መካከል ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ በህዝብ እና በህዝብ ተመራጮች መካከል የመጀመሪያ ጊዜ የመራጭ ተመራጭ ምክክር እየተደረገ ነው፡፡
በከተማዋ የብልፅግና ፓርቲን በመወከል ተመርጠው ወደ ፌዴራል እና ክልል ምክር ቤቶች የገቡት የፌዴራል እና የክልል የህዝብ ተመራጮች ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን በመቀበል እና በማወያየት ውይይቱን መርተዋል።
ተወያዮቹ በርካታ ጥያቄዎችን በመድረኩ ማንሳታቸውን ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የህወሀት አሸባሪ ቡድን ላይ መንግስት አስቸኳይ እርምጃ በመውሰድ ከአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች እንዲወጣ እና ሙሉ ለሙሉ እንዲወገድ ቢደረግ በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እርማትና የመግቢያ ውጤት እንዲስተካከልም ህብረተሰቡ ለከተማዋ ተመራጮች ጥያቄ አቅርቧል፤ እንዲሁም ከሀገር አቀፍ ችግሮች በተጨማሪም የጎንደር ከተማ ሰላምና ልማት ጉዳይም በውይይቱ ላይ የተነሱ ጥያቄዎች መካከል ይጠቀሳል።
ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የህዝብ ተመራጮች አብዛኛቹ ችግሮች የተፈጠሩት ሃገሪቱ በህልውና አደጋ በተወጠረችበት ወቅት መሆኑን በመገለፅ ከህዝቡ የተነሱ ጥያቄዎች መፈታት ያለባቸው ጉዳዮች እንደሆኑ እናምናለን ፤ከዞን ጀምሮ እስከ ፌደራል ላሉ የመንግስት መዋቅራዊ አካላት እንደሚያቀርቡና መፍትሄ እንዲመጣም እንጠይቃለን ሲሉም ቃል ገብተዋል።
በኤልያስ አንሙት
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!