ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ
ለሁለት ቀናት የሚቆየው የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ÷ በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግሮች፣ ህዝብን ለከፍተኛ ምሬት እየዳረገ የሚገኘው የኑሮ ውድነት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚታዩ ችግሮች ላይ ውይይት በማድረግ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ ባለፈም ጉባኤው በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ ያሉ አበረታች እና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ ውይይት የሚያደረግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በህግ የበላይነት፣ በህዝብ ሰላም እና ደህንነት እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይ ጉባኤው በትኩረት ተወያይቶ የወደፊት አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥም ተገልጿል፡፡
የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች እና ደምቦች እንዲሁም የተለያዩ ሹመቶች ለጉባኤው ቀርበው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ውሳኔ ይፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱራህማን ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፥ በክልሉ ባለፋት ሰባት ወራት የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን ገልጸው÷አሁንም ሌተቀን ልንሰራባቸው የሚገባ ጉዳዮች ከፊታችን ይጠብቁናል ብለዋል።
ባለፉት ጊዜያት የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት የማይፈልገው ሸኔ ያደረሰውጉዳት ትልቅ መሆኑን አፈ ጉባኤዋ አንስተዋል፡፡
አሸባሪው ሸኔ እያደረሰ ያለው ጉዳት አስቸኳይ እልባት ይፈልጋና ያሉት አፈ ጉባኤዋ፥ ለዚህም የፀጥታ መዋቅሩ ከህዝቡ ጋር በመሆን በተቀናጀ መልኩ መንቀሳቀስ ይገባል ነው ያሉት።
በክልሉ የመሬት ዝርፊያ እና ህገወጥ ግንባታዎች በከተሞች አከባቢ ጎልቶ የሚታይ በመሆኑ ይህም እንዲቀረፍ ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ ያነሱት ወ/ሮ ሰዓዳ፥ ከኑሮ ውድነት ጋር የሚገናኙ ጉዳዮች ላይ በስፋት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
በክልሉ የተከሰተው ድርቅ በእንሰሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ያሉት አፈ ጉባኤዋ፥ በሰዎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ውጤታማ ስራዎች ቢሠሩም አሁንም ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት።
በአፈወርቅ አለሙ፣ ዳግማዊ ዴክሲሳ እና ገመቺስ ታሪኩ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!