Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የዓለም የውሃ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሴኔጋል ገቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በ9ኛው የዓለም የውሃ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሴኔጋል ገቡ፡፡
 
በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመራ እና የውሀ እና ኢነርጂ ሚንስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋን ያካተተው የልዑካን ቡድን በ9ኛው የዓለም የውሃ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዳካር ገብቷል።
 
“የውሃ ደህንነት ለሰላምና ልማት” በሚል መሪቃል በሴኔጋል ዳካር የሚካሄደው 9ኛው የዓለም የውሃ መድረክ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ውሳኔ ሰጪዎች፣ የባለብዙ ወገን ተቋማት፣ ሲቪል ማህበረሰብ እና የግሉ ዘርፍን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙበት ኢቢሲ ዘግቧል።

በየሶስት አመቱ የሚካሄደው የዓለም የውሃ ፎረም በዓለም አቀፍ ደረጃ በውሃ እና በንፅህና አገልግሎት ረገድ እጅግ አንገብጋቢ የሆኑ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ከሰሃራ በታች ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው የውይይት መድረክ ትኩረት ድንበር ተሻጋሪ ውሃማ አካላት ዘላቂ እና ሰላማዊ አጠቃቀም እና ለጸጥታ፣ መረጋጋት እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ያላቸው ጠቀሜታዎች እንዲሁም በድርቅ እየተጎዱ ባሉ የዓለም ክልሎች ላይ ይሆናል ተብሏል።

በዚህ መድረክ ለመሳተፍ ሴኔጋል ዳካር የገቡት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴም በመድረኩ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.