ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የዓለም የውሃ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሴኔጋል ገቡ
በየሶስት አመቱ የሚካሄደው የዓለም የውሃ ፎረም በዓለም አቀፍ ደረጃ በውሃ እና በንፅህና አገልግሎት ረገድ እጅግ አንገብጋቢ የሆኑ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ከሰሃራ በታች ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው የውይይት መድረክ ትኩረት ድንበር ተሻጋሪ ውሃማ አካላት ዘላቂ እና ሰላማዊ አጠቃቀም እና ለጸጥታ፣ መረጋጋት እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ያላቸው ጠቀሜታዎች እንዲሁም በድርቅ እየተጎዱ ባሉ የዓለም ክልሎች ላይ ይሆናል ተብሏል።
በዚህ መድረክ ለመሳተፍ ሴኔጋል ዳካር የገቡት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴም በመድረኩ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።