Fana: At a Speed of Life!

የጨፌ ኦሮሚያ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችንና ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጨፌ ኦሮሚያ አንደኛ አመት 2ኛ መደበኛ 6ኛ የስራ ዘመን የተለያዩ አዋጆችንና ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቋል፡፡

በአዳማ ገልማ አባ ገዳ አዳራሽ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ጉባኤ፥ የመንግስት የልማት ድርጅት አስተዳደርን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ላይ ውይይት በማድረግ አጽድቋል፡፡

አዲሱ አዋጅ ከተቋማቱ ብዛት፣ አይነትና ወቅታዊነትና የገበያ ሁኔታ አንፃር ተሻሽሎ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ልማት ድርጅት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 243/2014 በመሆን በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡

የክልሉን ማህበረሰብ የመረዳጃ ስርዓት ለማጠናከር የኦሮሚያ ክልል የቡሳ ጎኖፋ አዋጅን በአብላጫ ድምፅ ስራ ላይ እንዲውል ጉባኤው ተዋያይቶ አጽድቋል፡፡

በተጨማሪም የኦሮሚያ ክልል ጋቸነ ሲርና አዋጅ ለማፅደቅ የወጣ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ በአብላጫ ድምፅ አጽድቆታል ፡፡

በሌላ በኩል ጉባኤው የተጓደሉ የጨፌውን ቋሚ ኮሚቴ አባላትንና የክልሉ ህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ኮሚቴ አባላትን በመሾም ጉባኤውን አጠናቋል፡፡

የተጓደሉ የክልሉ ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች አጣሪ ኮሚቴ ለመሙላት አቶ ዘሪሁን ዱጉማ ተሹመዋል።

የተጓደሉ የጨፌ ቋሚ ኮሚቴ አባላትን ለመሙላት ደግሞ

1 አቶ ግርማ ታረቀኝ – የአስተዳደር፣ ህግና የሰው ሃብት ልማት ቋሚ ኮሚቴ አባል

2 አቶ ገልማ ዋቆ – የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል

3 ወይዘሮ ሰአዳ ኢብራሂም – የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል

4 አቶ ሃሩን ኦብሳ – የበጀትና የመንግስት ንብረት አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ አባል

5 አቶ ከበደ ዴሲሳ – የአስተዳደር፣ ህግና የሰው ሃብት ልማት ቋሚ ኮሚቴ አባል

6 አቶ ሲራጅ አብዱሮ – የከተማ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ተሹመዋል።

በአፈወርቅ አለሙ እና ዳግማዊ ዴክሲሳ

ተጨማሪ መረጃ ከጨፌ ኦሮሚያ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.