በደቡብ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ድህረ ጉባዔ የህዝብ ውይይት መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ድህረ ጉባዔ የህዝብ ውይይት በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ነው፡፡
በደቡብ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ያሳለፋቸው ውሳኔዎችና አቋሞች ላይ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችል ህዝባዊ የውይይት መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እርስቱ ይርዳ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የጋሞ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
የህብረተሰብ አቀፍ የውይይት መድረኩ አብይ ዓላማ የህዝቡን ጥያቄ ለማድመጥ እና የብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ በመከረባቸዉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ህዝቡ ግልጽነት እንዲፈጥርባቸው ለማድረግ እንደሆነም ተገልጿል።
በፓርቲው አቋሞች እና ውሳኔዎች ላይ በመምከር የጋራ መግባባት ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።
በተጨማሪም በወላይታ ሶዶ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ በጉባዔው ውሳኔዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከነዋሪዎች ጋር እየተወያየ ነው።
መድረኩ ሕዝቡ የሚያነሳቸውን ወቅታዊና አንገብጋቢ ጥያቄዎች ከጉባዔው አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውንና በየደረጃው ያሉ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የጋራ መግባባት ለመድረስ ያለመ ነው ተብሏል፡፡
በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጨምረው የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ፣ ሌሎች አመራሮችና ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡
በማስተዋል አሰፋ
ተጨማሪ መረጃ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!