Fana: At a Speed of Life!

የሮታ ቫይረስ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መከሰቱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 14፣2014(ኤፍ ቢሲ) የሮታ ቫይረስ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኩርሙክ፣ በሸርቆሌ ወረዳ እና አሶሶ ከተማ መከሰቱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
ቫይረሱ በአብዛኛው ህጻናት ላይ የሚከሰትና ለሞት የሚዳርግ በመሆኑ ህብረተሰቡ የአካባቢውንና የግል ንጽህናውን በአግባቡ መጠበቅ እንዳለበት ቢሮው አሳስቧል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች አስተዳደር ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ፍቃዱ አያሌው እንዳሉት የሮታ ቫይረስ በክልሉ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ መከሰቱን ገልጸው ቫይረሱ ትኩሳት፣ ትውከትና የተቅማጥ ምልክት የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል፡
ቫይረሱ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያጠቃ ቢሆንም ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናትን ለከፋ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን ያስታወቁት አቶ ፈቃዱ በንክኪ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
ቫይረሱ በክልሉ ሞቃታማ በሆኑ አካባቢዎች ላይ በየአመቱ እየተከሰተ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ቢሮው በሽታው እንዳይከሰት ቀድሞ የመከላከል ሲከሰት ደግሞ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡
አሁን ላይ ቫይረሱ 549 ህጻናት ላይ መገኘቱን ነው አቶ ፈቃዱ የገለጹት፡፡
ህብረተሰቡ የህጻናትንና የራሳቸውን ንጽህና በአግባቡ ከመጠበቅ ባሻገር ምልክቱ ሲከሰት ቶሎ ወደ ህክምና መሄድ እንዳለባቸው ቢሮው ማስታወቁን የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.