Fana: At a Speed of Life!

የጋራ ችግሮችን ለመፍታት በትብብር መስራት አስፈላጊ ነው -ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋራ ችግሮችን ለመፍታት በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።
በሴኔጋል ዳካር እየተካሄደ በሚገኘው የመሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የፓርላማና ሲቪል ማህበረሰብ አባላት፣ የግል ሴክተር፣ ምሁራን 9ኛው “ዓለም አቀፍ የውሃ ፎረም” ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ተሳትፈዋል።
ፕሬዚዳንቷ በንግግራቸው ስለ ህዳሴ ግድብና አረንጓዴ አሻራን በተመለከተ አንስተዋል።
እንዲሁም የጋራ ችግሮችን ለመፍታት የተያያዙ ሶስት ዋና ዋና አካሄዶችን፥ የፓለቲካ ቆራጥነት፣ ውሃ የቴክኒክ ጉዳይ ስለሆነ የፖለቲካ ገጽታ ሊሰጠው እንደማይገባ እንዲሁም የትብብር አስፈላጊነትን አብራርተዋል።
በሴኔጋል መንግሥትና በዓለም የውሃ ምክር ቤት ትብብር የተዘጋጀው ይህ ፎረም በ1997 ከተቋቋመ ወዲህ በየሶስት ዓመቱ ሲካሄድ መቆየቱን ከፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.