Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳ በጋሞ ዞን በካምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ጎበኙ

አዲስ አበባ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በጋሞ ዞን በካምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድንገተኛ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በጋሞ ዞን በካምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በነበራቸው ጉብኝት÷ በሆስፒታሉ እየተከናወነ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ተመልክተዋል።
የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር በረከት ተሰማ እንደገለጹት÷ የጨቅላ ሕጻናት ማሞቂያ እና ማቆያ ክፍል እንዲሁም የህክምና መስጫ ቁሳቁሶች እጥረት በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል።
በተለይም የኬሚስትሪ፣ የሰመመን መስጫ፣ የልብስ ንጽህና መስጫ ማሽኖች እና ሌሎችም ችግር መኖሩንም ገልጸዋል፡፡
የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በበኩላቸው÷ ሆስፒታሉ በ2010 ዓ.ም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ጠቁመው÷ በወቅቱ ኅብረተሰቡ አገልግሎቱን ለማግኘት ከነበረው ጉጉት አኳያ ሆስታሉ በቂ ቁሳቁስ ሳይሟላለት ሥራ መጀመሩን አንስተዋል፡፡
አያይዘውም ከአገልግሎት ፈላጊው ሕዝብ ቁጥር አንጻር የኅብረተሰቡን የጤና ተደራሽነት ማሳደግ አለመቻሉን አስረድተዋል፡፡
የንጹህ መጠጥ ውኃ፣ የመብራት መቆራረጥ እንዲሁም የኃይል መስጫ ጀኔሬተር እጥረት መኖሩንም አስረድተዋል።
የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ÷ የክልሉ መንግሥት ሆስፒታሉ ያጋጠመውን የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ለማሟላት ይሠራል ብለዋል፡፡
በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በሚገኙ የጤና ተቋማት የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት መኖሩን ጠቁው÷ በካምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተስተዋለው መሰረታዊ የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ቅድሚያ ተሰጥቶት ለመቅረፍ ጥረት ይደረጋል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.