Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ከውስጥ እና ከውጪ የሚቃጡ ጥቃቶችን የሚመክት ባህር ኃይል እየተገነባ ነው – የባህር ኃይል ዋና አዛዥ 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገራችን ከውስጥ እና ከውጪ የሚቃጡ ጥቃቶችን የሚመክት ባህር ኃይል እየተገነባ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ዋና አዛዥ ሬር አዲሚራል ክንዱ ገዙ ተናገሩ።
ዋና አዛዡ በቢሾፍቱ የሚገኘውን የባህር ሃይል መሠረታዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የስራ እንቅስቃሴንና እየተገነባ ያለውን ህንፃ ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ ከተማሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱም ዋና አዛዡ የሀገርን ደህንነት ማስጠበቅ የሚችል፣ ከውስጥ እና ከውጭ የሚመጡ ችግሮችን የሚመክት ዘመናዊ ባህር ኃይል መገንባትና ማሰልጠን አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የባህር ኃይልን አቅም ለማሳደግ የተማረ፣ የሰለጠነ፣ ስነ ምግባር ያለው እና ሀገሩን የሚወድ ቁርጠኛ የሆነ የሰው ኃይል ያስፈልጋል” ያሉት ሬር አዲሚራል ክንዱ÷ ባህር ኃይልን ወደ ቀድመ ክብሩ ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ዋና አዛዡ ለባህር ኃይል ተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያ ከባህር ኃይል ማግኘት የምትችለውን ጥቅም እንድታገኝ በሀገር ውስጥና በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚሰጣቸውን ሥልጠና በብቃት መወጣት ይገባቸዋል ማለታቸውንም ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.