Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የጓሮ አትክልት ንቅናቄን አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ “ምግባችን ከጓሮዋችን” በሚል መሪ ቃል የጓሮ አትክልት ልማት ንቅናቄን በይፋ አስጀምረዋል፡፡
 
በአንድ አርሶ አደር ማሳ በመገኘት የጓሮ አትክልት ንቅናቄውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት የከተማ አስተዳደሩ የከተማ ግብርናን ለማስፋፋት ለየት ያለ እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል፡፡
 
የከተማ ግብርና በብዙ ታላላቅ ሃገራት የተለመደ መሆኑን አውስተው በእኛ አገር ደግሞ በብዙ መንገድ የተሸልን በመሆናችን ትንሽ ግብአትና ስልጠና ብናክልበት የከተማ ግብርናን ማስፋፋት እንችላለን ብለዋል።
 
በተለይም ለአዲስ አበባ አትክልትና ፍራፍሬ ከሩቅ ቦታ እንደምታገኝ አስታውሰው ፤በዚህ ሂደት ከተማ እስኪደርስ ተበላሽቶ ከመድረሱም በላይ ዋጋውን እንደሚያንረው መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.