Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ ምክር ቤትና አስፈፃሚው አካል የዕቅድ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትና በአስፈፃሚው አካል መካከል የእቅድ ስምምነት የፊርማ ስነ ስርዓት ተከናወነ፡፡
የስምምነት ፊርማው ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈጉባኤ ቡዜና አልቃድር በተገኙበት መካሄዱን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሕዝቡን ውክልና ሥራዎችና አስፈፃሚውን የመከታተልና የመቆጣጠር በአግባቡ መሥራት እንዲያስችለው ቋሚ ኮሚቴዎችን አደራጅቶ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወቃል፡፡
ምክር ቤቱ አስፈፃሚውን አካል የመከታተልና መቆጣጠር ስልጣኑን ተግባራዊ ለማድረግ ብሎም የተጠያቂነትን ስርዓት ለማስፈን እንዲረዳው÷ በምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎችና በአስፈፃሚው አካላት (የቢሮ ሃላፊዎች ) መካከል የተቋማቱን ዕቅድ መሠረት ያደረገ የስምምነት ፊርማ ነው የተካሄደው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት እንደገለጹት÷ ዛሬ የተካሄደው ስምምነት ለይስሙላ የሚደረግ ሳይሆን አስፈጻሚውን አካል ለመቆጣጠር የሚያስችል ዓላማ ያነገባና ስራን በተገቢው መንገድ ለማከናወን የሚያስችል ነው፡፡

ምክር ቤቱና ሕዝባችን የጣለሉብንን ኃላፊነት በተሟላ አግባብ እንድንፈጽም የሚያስችል የተጠያቂነት ስርዓትን ከንግግር ባለፈ መሬት ላይ ለማውረድ የሚረዳ፤ የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ እንድናቀርብ የሚያስችለንም ነው ብለዋል፡፡

ዛሬ በተፈረመው ስምምነት መሰረት የሕዝብ ተወካዮች አስፈፃሚውን አካል በየጊዜው በመከታተል፥ በመቆጣጠርና በመደገፍ የከተማዋን ዕድገት፣ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ ሊሠሩ እንደሚገባ መናገራቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.