Fana: At a Speed of Life!

የቴክኖሎጂ ፈጠራ ማበልፀጊያ ማዕከል ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮርያ መንግስት ድጋፍ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራ ማበልፀጊያ ማዕከል ሊገነባ እንደሆነ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የኮርያ አለም አቀፍ ኮኦፕሬሽን ኤጀንሲ በቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራ ማበልፀጊያ ማዕከል ግንባታና ድጋፍ ዙሪያ መክረዋል።

ማዕከሉ በኮርያ መንግስት ድጋፍ በ600 ሺህ ዶላር ወጪ በአይ ሲ ቲ ፓርክ ውስጥ የሚገነባ ሲሆን የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤቶች የፈጠራ ስራዎቻቸውን የሚያበለፅጉበትና ወደ ንግድ የሚለውጡበት ነው ተብሏል።

በኮርያ አለም አቀፍ ኮኦፕሬሽን ኤጀንሲ ድጋፍ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እስከ 2025 የሚቆይ የ10 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ተቀርፆ እየተተገበረ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ በዚህ ፕሮጀክት እየተደገፉ ያሉና ተወዳድረው ለተመረጡ 10 ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች እስከ 5 ሺህ ዶላር የሚደርስ የመነሻ ገንዘብ ተሰጥቷቸው በቅርቡ ይመረቃሉ ብለዋል።

የኮይካ የኢትዮጵያ ምክትል ተወካይ ሺንያንግ ሊ በበኩላቸው የኮርያ መንግስት በኢትዮጵያ የፈጠራ ስራ እንዲዳብር ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የዲዛይን ስራው የተጠናቀቀው ማዕከሉ የውስጥ እድሳት ስራ፣ የፈጠራ የንድፍ ስራ መሳሪያዎች፣ ባለሙያዎች እና አስፈላጊ መሳሪያዎች ይሟሉለታል መባሉን ከሚኒስቴሩ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.