Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በወረራ የደረሰበትን ውድመት ለመታደግ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወሎ ኦሮሞ ልማት ማህበር የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በአሸባሪው ቡድን ወረራ ውስጥ በነበረበት ወቅት የደረሰበትን ውድመት ለመታደግ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ እያካሄደ መሆኑ ተገለጸ።

በገቢ ማሰባሰቢያ መድረኩ ላይ የተገኙት የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አስተዳዳሪ አህመድ አሊ፥ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ወደ ዞኑ በወረራ ከመግባቱ በፊትም ሆነ በኋላ ህዝቡ ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጉን ገልፀዋል።

ዞኑ በህወሃት የሽብር ቡድን ወረራ ውስጥ በነበረበት ወቅትም ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ውድመት ደርሶበታል ያሉት አስተዳዳሪው፥ አጎራባች ዞኖችም ሆኑ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሽብር ቡድኑ ለደረሰብን ችግር ከጎናችን በመቆም አጋርነታቸውን አሳይተዋል ብለዋል።

የዛሬው የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ አንዱ ዓላማ ከምሁራን ፣ ከዳያስፖራና ከአጋር አካላት ጋር በመሆን በዞኑ ነባራዊ ሁኔታ ላይ ምክክር ለማድረግ መሆኑን የገለፁት የዞኑ አስተዳዳሪ፥ ሁለተኛው ዓላማ ደግሞ የሥነ ልቡና ስብራት ለደረሰባቸውና ሀብት ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች አለኝታነታችንን ለማሳየት ነው ብለዋል፡፡

በገቢ ማሰባሰሰቢያ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአማራ ብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር፥ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ልማቱን ለማፋጠን በሚያደርገው ጥረት ሰላም አስፈላጊ በመሆኑ የሰላሙ ዋነኛ ባለቤት የሆነው ህብረተሰቡም የበኩሉን ገንቢ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል።

የተጎዳውን ልብና የወደመውን ንብረት መጠገን እና አብልጦ መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል አቶ ግርማ የሺጥላ፡፡

 

በአለምሰገድ አሳየ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.