Fana: At a Speed of Life!

ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ለሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ ማረፊያ ቦታ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ለሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የማረፊያ ቦታ መዘጋጀቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን በጊዜያዊነት የሚያርፉበት ቦታ በተለምዶ ወሰን ሁለት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ከስደት ተመላሾች ጊዜያዊ ማቆያ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ነው የተዘጋጀው፡፡

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ከስደት ተመላሾች ጊዜያዊ ማቆያ ቅጥር ግቢ በመገኘት ተመላሾችን ለመቀበል የተሰሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ተግባራት እንደሚሠሩም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.