Fana: At a Speed of Life!

በጉራጌ ዞን በደረሰ የእሳት አደጋ 42 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በጉራጌ ዞን ቀቤና ወረዳ በሌንጫ ቀበሌ በደረሰ የእሳት አደጋ 42 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገለፀ።

በጥንቃቄ ጉድለት በአካባቢው የነበረውን ቁጥቋጦ ለማጥፋት በሚል የተለኮሰ እሳት በወቅቱ በነበረ ከፍተኛ ንፋስ ወደ አካባቢው በመዛመቱ ነው የእሳት አደጋው የደረሰው።

በቀቤና ወረዳ በሌንጫ ቀበሌ ልዩ ስሙ ፈረጀቴ ጎጥ ትናንት እኩለ ቀን ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ 35 የሳር ክዳን ቤቶች፣ 5 የቆርቆሮ ክዳን ቤቶችና 2 መስጂዶች በድምሩ 42 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገልጿል።

2ቱ መስጂዶች በከፊል የወደሙ ሲሆን÷ በምርትና በሰብል ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱም ተመላክቷል።

የቀቤና ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት በበኩሉ ÷ወቅቱ ነፋሻማ በመሆኑ የወረዳው ማህበረሰብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስቧል።

ጉዳቱ የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ሁሉም ርብርብ ማድረግ እንደሚገባውም ፅህፈት ቤቱ ጥሪ ማቅረቡን ዴሬቴድ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.