Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩኣን ሐዋሳ ከተማን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩኣን የሐዋሳ ከተማን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ የከተማዋ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን ጨምሮ የከተማዋ የተለያዩ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
አምባሳደሩ በከተማዋ ያሉ የልማትና የኢንቨስትመንት ስራዎችን መመልከታቸውን ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በማህበራዊ ትስሰር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡
ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ካላት የጠበቀ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት በዘለለ ባለሃብቶቿ በተለያዩ ግዙፍ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ በመሰማራትና መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል መፍጠራቸውን ከንቲባው አውስተዋል፡፡
ሐዋሳም ካላት ምቹነት በመነሳት ቀጣይ የትኩረት ማረፊያ በምትሆንባቸው ጉዳዮችና ድጋፎች ዙርያ ውይይት መካሄዱን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም ያሉ አማራጮችና ለከተማዋ ልዩ ፋይዳ ባላቸው ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉ ተመላክቷል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.