Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የበጋ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን ማጠናከር ይገባል- ኢ/ር አይሻ መሀመድ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የበጋ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን ማጠናከር እንደሚገባ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ገለጹ።
ሚኒስትሯ በሐረሪ ክልል ኤረር ወረዳ በበጋ መስኖ ልማት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን የጎበኙ ሲሆን÷ በዚህም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች አበረታች ናቸው ብለዋል፡፡
ጥልቅ ውሃ ጉድጋዶችን በመቆፈርና የመስኖ ውሃን በመጠቀም የተለያዩ የምግብ ሰብሎችን ምርት የማምረት ተግባሩ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ነው ያመላከቱት፡፡
በክልሉ አርሶ አደሩ የምግብ ሰብልና ሌሎች ምርቶችን በስፋት ማምረት እንዲችል የውሃ ግድብ ፕሮጀክቶችን ማስፋፋት እንዲሁም በቴክኖሎጂና በግብዓት መደገፍ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
የጉብኝቱ አላማ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመስኖ ውሃ ፕሮጀክቶችን ለማከናወንና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ናቸው፡፡
የውሃ ግድች መገንባት አርሶ አደሩን ከዝናብ ጠባቂነት በማላቀቅ በአመት 3 ጊዜ ምርቶችን እንዲያመርት ያስችላልም ብለዋል፡፡
በጉብኝቱ የተሳተፉት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቶ አለልኝ አድማሱ÷ እስራኤልና ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ያላቸው ትስስር ጠንካራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አምባሳደሩ እስራኤል በኢትዮጵያ ለሚገኙ ክልሎች በግብርናው ዘርፍ ያላትን ልምድ ለማካፈልና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚከናወኑ ተግባራት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራች መሆኗን አብራርተዋል፡፡
በቀጣይም እየተከናወኑ በሚገኙ የግብርና ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.