በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች በከፈቱት ተኩስ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ አውራ ጎዳና እየተባለ በሚጠራው አከባቢ ትላንት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች በከፈቱት ተኩስ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል፡፡
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ቦስት÷በሰው ህይወትና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት እስካሁን በውል አለመታወቁን ገልጸው÷ አካባቢው የጸጥታ ስጋት ቀጠና እየሆነ በመምጣቱ በየጊዜው መሰል የፀጥታ ችግሮች እየተፈጠሩ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
ትላንት የተፈጠረው ችግርም ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን ያነሱት አስተዳዳሪው÷ ታጣቂዎቹ በተሽከርካሪ ወደ ቀበሌው በመግባት ከባድ መሳሪያ ወደ ህዝቡ በመተኮስ በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የጸጥታ ሀይሎች ወደ አካባቢው በመግባታቸው የተኩስ ድምጽ መቀነሱን ጠቁመው÷ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ በቀጣይ ተጣርቶ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በአይናለም ስለሺ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!