Fana: At a Speed of Life!

የዘላቂ ልማት ግቦች አስተዳደር ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘላቂ ልማት ግቦች አስተዳደር ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ይፋ ተደርጓል፡፡
ፕሮጀክቱ በአዲስ አበባ ፣ በኦስሎ እና በማላዊ ዩኒቨርሲዎች በጋራ የተከፈተ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገረመው ነጋሳ ኢትዮጵያ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በአሁኑ ጊዜ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የ10 አመት የልማት እቅድ እየተገበረች እንደምትገኝ ገልጸዋል።
ይህንኑ የልማት ግብ ለመምራት እና በተገቢው መንገድ ለማሳለጥ በአገር አቀፍ ደረጃ ግብረ ኃይል መቋቋሙንም አስታውሰዋል፡፡
በዚሁ ግብረ ኃይል የተቋቋመው ኮሚቴ በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር እና በተባበሩት መንግስታት ጥምረት ሲመራ እንደነበር አስታውሰው፥ ስትራቴጂ በመቅረጽ፣ ፖሊሲ በመንደፍ እንዲሁም አጠቃላይ ሒደቱን ሲገመግም መቆየቱን ተናግረዋል።
ግምገማው በድህነት ቅነሳ በማድረግ፣ በጾታ እኩልነት፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ እና ንጽህና፣ በትምህርት ጥራት እና ተቋማዊ ጥንካሬ ዘርፎች ጉድለት መገኘቱን አመላክተዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጥምረት ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው የገለጹት ኃላፊው፥ ለፕሮጀክቱ ግቦች መሳካትና እንደ ሀገር ለሚያበረክተው አስተዋጽኦ ድጋፍ ያደርጋል ማለታቸውን ከፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.