Fana: At a Speed of Life!

ከ171 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ171 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ባሳለፍነው ሳምንት ባደረገው ክትትል 166 ሚሊየን 194 ሺህ ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 5 ሚሊየን 226 ሺህ ብር የሚያወጡ የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መያዛቸውን አሳውቋል፡፡
የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ሞያሌ እና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ÷ በቅደም ተከተላቸው 28 ነጥብ 2 ሚሊየን፣ 23 ነጥብ 6 ሚሊየን እና 22 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ እንደቻሉ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 8 ሰዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች ውስጥ አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.