መንግሥት የዋጋ ንረቱን ለመቋቋም የሚያስችሉ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት የዋጋ ንረትን እና የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም የሚያስችሉ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት መንግሥት ባስቀመጠው የመፍትሄ አቅጣጫ መሰረት የአጭር ጊዜ፣ የመካከለኛ እና የረዥም ጊዜ ዕቀድ በማውጣት እየሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡