Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 7ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎች ማሳለፉን አስታወቀ፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 7ኛ መደበኛ ስብሰባ÷ በማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏ፡፡
ምክር ቤቱ በመካከለኛ ዘመን (2014-2019) የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ የተወያየ ሲሆን÷ የማዕቀፉ ዋና ዓላማ የ2015 የፌዴራል መንግስት ዝርዝር በጀት የሚዘጋጅበትና ጥቅል የገቢ ትንበያ፣ የወጪ ጣሪያ፣ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት የበጀት ድጋፍ ጣሪያ እና የፊሲካል ጉድለት መጠንን በማዕቀፍነት መወሰን ነው፡፡
ማዕቀፉ በዋናነትም ለተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች፣ ለተከሰቱ የሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ሰብዓዊ ድጋፍ፣ ለመልሶ ግንባታና ማቋቋም፣ ለአገር መከላከያ፣ ለእዳ ክፍያ እና ለአዳዲስ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚያስፈልገውን የወጪዎች መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡
ምክር ቤቱ በማዕቀፉ ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን አክሎ በማጽደቅ ስራ ላይ እንዲውል መወሰኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.