የቱርኩ ኩባንያ ከሚያልፉ ተሽከርካሪዎች የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያመነጭ ማሽን አስተዋወቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንገድ ላይ ከሚያልፉ ተሽከርካሪዎች የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት የሚችል ማሽን በቱርክ ኩባንያ ተሰርቷል፡፡
በቱርክ ዲ ቪ ሺ ቴክ በተሰኘው ኩባንያ የተመረተው ይህ ማሽን ተንቀሳቃሽ ተርባይን ያለው ሲሆን መንገድ ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች የሚፈጥሩትን ንፋስ ወደ ኤለክትሪክ ሀይል መቀየር የሚችል ነው ተብሏል፡፡
የማሽኑ ተርባይን የተሽከርካሪዎችን የነፋስ ሀይል ወደ ኤሌክትሪክ ሀይል ከመቀየር በተጨማሪ በከባቢ አየር ላይ ያለውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን መለካት የሚችል መሆኑም ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ተርባይኑ ከተሽከርካሪዎች የሚያገኘውን ነፋስ በመጠቀም በሰዓት 1 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት ይችላል ነው የተባለው፡፡
ማሽኑ በቱርክ ኢስታንቡል ከተማ ሙከራ ማድረጉን የዩኒላንድ መረጃ ያመላክታል።
ይህ አስገራሚ ፈጠራ በማንኛውም ቦታ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች የሚፈጥሩትን ንፋስ ወደ ታዳሽ ሀይል ምንጭነት እያዋለ ስለመሆኑም መረጃው አመላክቷል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!