Fana: At a Speed of Life!

ባለሥልጣኑ ስርዓተ ፆታን ያገናዘበ የግጭት አዘጋገብ መመሪያ ላይ እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ሴቶች ጋር በመተባባር ስርዓተ ፆታን ያገናዘበ የመገናኛ ብዙኃን የግጭት አዘጋገብ መመሪያ አዘጋጅቶ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር እየተወያየ ነው፡፡

የውይይቱ ዋና ዓላማ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ከግጭት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ዘገባዎች በሚዘግቡበት ጊዜ ስርዓተ ፆታ ላይ የተመረኮዙ ጅምላ ፍረጃዎችን፣ የተዛቡ ስርዓተ ፆታዊ አስተሳስቦችን እና አድሎዎችን እንዲያስወግዱ እንዲሁም ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ የግጭት ዘገባ አቀራርቦችን እንዲገነዘቡ እና መመሪያውን ተከትለው እንዲሰሩ ለማድረግ ነው፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ እንደተናገሩት ፥ የፆታ እኩልነት የወንዶችና ሴቶችን ድምፅ በእኩል መጠን ለማስተናገድ እንዲያመች ስርዓተ ፆታን ያገናዘበ የግጭት አዘጋገብ መመሪያ ተዘጋጅቷል።

በመሆኑም ይሄን ለማስፈፀም የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም ለባለሙያዎቹ ተከታታይ የሆነ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልፀው ፥ ተሳታፊዎቹ ከስልጠናው ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚያስችላቸውን ልምድ እንደሚያገኙበት ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.