ክላረንስ ሲዶርፍ ከታላቁ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ጋር አዲስ አበባ ገብቷል
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የሪያል ማድሪድ እና ኤሲ ሚላን ኮኮብ ክላረንስ ሲደሮፍ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ጋር አዲስ አበባ መጥቷል፡፡
በአፍሪካ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ጉዞ ከሚያደርግባቸው አራት አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ባለ ትልቁ ጆሮ ዋንጫ ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል ለዕይታ በቅቷል ።
ከዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ሞዛምቢክ በመቀጠል የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ጉዞውን ወደ ኢትዮጵያ ያደረገ ሲሆን አራት ጊዜ ከሶስት የተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች ጋር ዋንጫውን ያነሳው ክላረንስ ሲዶርፍ ደግሞ ዋንጫውን ይዞ አዲስ አበባ ደርሷል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በስፍራው በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
በሀይኒከን ኢትዮጵያ አማካኝነት ይህንን የተከበረ ዋንጫ ወደ ኢትዮጵያ ይዞ የመጣው ክላረንስ ሲዶርፍም ከደቂቃዎች በፊት ከብዙሃን መገናኛ አባላት ጋር የጥያቄ እና መልስ ቆይታ አድርጓል፡፡
ክላረንስ ሲዶርፍ በዛሬው ዕለት የወዳጅነት ፓርክን መጎብኘቱንም ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።