Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በጤናው ዘርፍ በትብብር ለመስራትና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከቻይና የበሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲ ዲ ሲ) ዳይሬክተር ጉው ፉ ጋር በበይነ መረብ ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም ሁለቱ አገራት በተለይ በበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ረገድ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
 
አምባሳደር ተሾመ ኢትዮጵያና ቻይና ያላቸውን ዘርፈ ብዙ ትብብርና ግንኙነት በውይይቱ አንስተዋል፡፡
 
ሀገራቱ በህክምናው ዘርፍ የሚያደርጉትን ትብብር አሁን ካለበት ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ በሁለቱም ወገን ከፍተኛ ፍላጎት ያለ መሆኑን ተናግረዋል።
 
በዚህም የቻይናው ሲዲሲ ከኢትዮጵያ አቻ የህክምና ተቋማት ጋር በሰው ሃይል አቅም ግንባታ፣ በጥናትና ምርምር ተቋማት ጉድኝት፣ በፋርማሴዩቲካል ኢንቨስትመንትና በህክምና ቴክኖሎጂ ልውውጥ በቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም ማዕቀፍ ተባብረው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
 
አምባሳደር ተሾመ አያይዘውም በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው የህክምና ተቋማት የመድሃኒትና የህክምና መርጃ መሳሪያዎችን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
 
ጉው ፉ በበኩላቸው÷ ቻይና እና ኢትዮጵያ በህክምናው ዘርፍ ጠንካራ ትብብር ያላቸው አገራት መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
 
በተለይ የአፍሪካ ሲዲሲ በአዲስ አበባ እየተገነባ መሆኑ የቻይና የበሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ከአፍሪካ አገራት ጋር በህክምናው ዘርፍ ለሚያደርገው የትብብር ስራ ኢትዮጵያን ማዕከል አድርጎ ለመጠቀም ምቹ እድል የሚፈጥርለት መሆኑን ተናግረዋል።
 
አምባሳደሩ ባቀረቧቸው ጉዳዮችና በሌሎችም ተያያዥ ዘርፎች ላይም በጋራ ለመስራትና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ አንደሆኑ መግለጻቸውን ከቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.