በሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በተከሰተ የእሳት አደጋ ከ160 በላይ መኖሪያ ቤቶች እና ሱቆች ወደሙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ ከ160 በላይ የሚጠጉ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን የወረዳው አስተዳዳደር አስታውቋል።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሀሰን ሀንዲ እንደገለፁት÷የእሳት አደጋው የደረሰው ትናንት 10 ሰዓት አካባቢ በድንገት ከቤንዚን መሸጫ ቤት በተነሳ እሳት ምክንያት ነው።
በደረሰው ድንገተኛ የቃጠሎ አደጋም እስካሁን ከ80 በላይ መኖሪያ ቤቶች እና 80 የሚሆኑ የተለያዩ የንግድ ሱቆች መውደማቸውን የገለጹት አስተዳዳሪው÷በሰው ህይወት ላይ የደረሰ አደጋ አለመኖሩን ጠቁመዋል፡፡
በአካባቢው ከፍተኛ ንፋስ በመኖሩ እና የውሃ እጥረት በማጋጠሙ ቃጠሎው በፍጥነት እንዲስፋፋ ማድረጉን ጠቁመው÷በዚህ ሳቢያም በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት መከሰቱን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም በተከሰተው የእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
በብዛት የቤንዚን ሽያጭ በሚከናወንባቸው ቦታዎች በቀላሉ የእሳት አደጋ እየተፈጠረ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የአፋር መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!