የጃፓን መንግሥት ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል- አምባሳደር ኢቶ ታካኮ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓን መንግሥት ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ተናገሩ።
የጃፓን መንግሥት ለሰላም ህጻናት መንደር የጨርቃ ጨርቅ ማሰልጠኛ ማዕከል የማስፋፊያ ግንባታ የሚውል 49 ሺህ ዶላር እንዲሁም 10 የስፌት ማሽንና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለማሰልጠኛ ተቋሙ ድጋፍ ማድረጉን በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ተናግረዋል።
በዚሁ ወቅት አምባሳደር ኢቶ እንደተናገሩት÷ የጃፓን መንግሥት ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብታዊ እድገትና የሰው ሀብት ልማት መሻሻል የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
የጃፓን መንግሥት ከ400 በላይ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በመሥራት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረጉን ገልጸው÷ በተለይም የጃፓን ልማት የትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) የበኩሉን እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሰላም ህጻናት መንደር የጨርቃ ጨርቅ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ጫሊ÷ የጃፓን መንግሥት ያደረገው ድጋፍ ተቋሙ በርካታ ሰው ተቀብሎ ለማሰልጠን ያስችለዋል ብለዋ፡፡
የተጠናቀቀው ይኸው የማስፋፊያ ግንባታም በዓመት 200 ተማሪዎችን በተጨማሪ ለማሰልጠን ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸው÷ በዚህም ለአገሪቱ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ዕድገት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!