የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለጅግጅጋ ከ15 ዓመት በታች ፓይለት ፕሮጀክት ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ለሚገኘው ከ15 ዓመት በታች ፓይለት ፕሮጀክት የኳስ እና የተለያዩ የስልጠና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡
የቁሳቁስ ድጋፉ በኢትዮጵያ አግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት በአቶ ኢሳያስ ጅራ አማካኝነት ተበርክቷል፡፡
አቶ ኢሳያስ ጅራ በጅግጅጋ የሚገኘውን ፕሮጀክት እንቅስቃሴ በመጎብኘት ታዳጊዎቹን ያበረታቱ ሲሆን በቆይታቸውም ከክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመላ ሀገሪቱ ከ15 ዓመት በታች ፓይለት ፕሮጀክቶች በማቋቋም በሁለቱም ፆታዎች በርካታ ታዳጊዎች ስልጠና በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!