በወልዲያ ከተማ ለ3 ሺህ ወገኖች የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወልዲያ ከተማ ለሚገኙ 3 ሺህ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ኤስ ኦ ኤስ የሕፃናት መንደሮች የአደጋ ጊዜ ምላሽ መስጠት ፕሮጀክት አስታወቀ፡፡
የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ጋሻዉ አለባቸው÷ ኤስ ኦ ኤስ የሕፃናት መንደሮች የአደጋ ጊዜ ምላሽ መስጠት ፕሮጀክት ዛሬ በ10 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የምግብ ነክ እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናትና አቅመ ደካሞች ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ ከዚህ በፊትም ለ1 ሺህ 641 ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናትና አቅመ ደካሞች ከ3ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች በበኩላቸው በፕሮጀክቱ ከዚህ ቀደም የቤት ቁሳቁስ ድጋፍ እንደተደረገላቸው አስታውሰው÷ በዛሬው ዕለትም ምግብ ነክ ድጋፍ ተደርጎልናል ማለታቸውን ከሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!