Fana: At a Speed of Life!

“ከዒድ እስከ ዒድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪን አስመልክቶ የበይነ መረብ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አደም መሃመድ በቱርክና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያውን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን ጋር “ከዒድ እስከ ዒድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪን አስመልክቶ በበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል።

አምባሳደሩ የሀገራዊ ጥሪውን ዓላማ እና ፋይዳ ለውይይቱ ተሳታፊዎች በዝርዝር በማስረዳት “ከዒድ አል ፈጥር እስከ ዒድ አል ዓድሃ ድረስ በዓላቱን በተለያዩ ዝግጅቶች በሀገር ቤት ለማክበር መንግስት ጥሪ ማድረጉን ተከትሎ፥ በሀገር ቤት ጉዞው ለሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተለያዩ መርሐ ግብሮች ይፋ መደረጋቸውን አስረድተዋል፡፡

ወደ ሀገር ቤት ለሚጓዙ እንግዶችም የኢትዮጵያ አየር መንገድም የ20 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አምባሳደር አደም አስረድተዋል።

በቀረቡት መርሐ ግብሮች ላይም ውይይት የተካሄደ ሲሆን ፥ የውይይቱ ተሳታፊዎች የቀረበው ሀገራዊ ጥሪ ትክክል መሆኑን የተቀበሉ መሆናቸውን ገለጸዋል።

በሀገራችን በግጭት እና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉም ነው የተናገሩት።

አምባሳደር አደም ዳያስፖራው እስካሁን ለሀገር እያደረገ ላለው ያላሰለሰ ድጋፍ እና እገዛ አመስግነው፥ ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ሀገራዊ ጥሪው ስኬታማ እንዲሆን እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በማብራራት በመርሐ ግብሩ ተሳታፊ ለሚሆኑ ኤምባሲው አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ ያደርጋል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዳያስፖራው በኩል ኮሚቴ ተቋቁሞ ከኤምባሲው ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑን እና በተለያየ ምክንያት ወደ አገር ቤት መሄድ ለማይችሉ ባሉበት ሆነው የተለያየ አስተዋጽኦ ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደርጓል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.