በአዲስ አበባ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጣለ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ጣለ፡፡
ወቅቱ የፋሲካ በዓል በመሆኑ ከፍተኛ የሰዎች እንቅስቃሴ ስለሚኖር፣ ግርግር እና ስርቆት እንዳይፈጠር በማሰብ፤ አዲሱ ጥናት ተጠናቆ እስኪጠናቀቅ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ ቁጥጥር እንዲደረግ እገዳ መጣሉን ነው ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በዚህም እርምጃ እንዲወሰድ ቢሮው ለሚመለከተው አካል የስራ ትዕዛዝ ማስተላለፉም ነው የተገለጸው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!