Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከአዲስ አበባ የታክሲ ባለንብረቶች ማኅበር አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአዲስ አበባ የታክሲ ባለንብረቶች ማኅበር አባላት ጋር ተወያዩ።

የታክሲ ባለንብረቶች ማኅበር አባላቱ ከውይይቱ ቀደም ብሎ ሸገርን የማስዋብ እና እንጦጦ ላይ እየተካሄዱ ያሉ ሥራዎችን ጨምሮ፥ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተጀመሩት የልማት ሥራዎች በኢንቨስትመንት አማካኝነት የመስፋፋት አቅም ያላቸው የትውልድ ሀብት መሆናቸውን ተናግረዋል።

አያይዘውም የመጓጓዣ አገልግሎት ሰጪዎች ከተለያዩ ሰዎች ጋር ከሚያደርጉት ግንኙነት የተነሣ የቱሪዝም እንቅስቃሴ እና የኢንቨስትመንት ፍሰት ላይ ዓይነተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው መናገራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ለብልጽግና ጎዳናን ለመጥረግ የራሳችንን ገደቦች አልፈን መጓዝ ከቻልን የሀገራችን ኢትዮጵያ ዕድገት አይቀሬ ነው ሲሉም ለማኅበራቱ አባላት አረጋግጠውላቸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.