Fana: At a Speed of Life!

የሞጆ ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ 88 በመቶ ተጠናቋል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሞጆ ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነው የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ 88 በመቶ ተጠናቋል።

ከሞጆ መቂ ከሚዘልቀው 56 ኪሎ ሜትር ውስጥ የ50 ኪሎ ሜትሩ ግንባታ መጠናቀቁን የግንባታ ሂደቱ በተጎበኘበት ወቅት ተገልጿል።

የሞጆ – ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ 201 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ከ13 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተይዞለታል።

የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ከአምስት ወራት በኋላ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የሞጆ ሃዋሳ የፍጥነት መንገድ በአራት ምዕራፍ ተከፍሎ ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል።

በዚህም ከሞጆ መቂ፣ ከመቂ ዝዋይ፣ ከዝዋይ አርሲ ነገሌና ከአርሲ ነገሌ ሃዋሳ የፍጥነት መንገዱ ግንባታ እየተከናወነ ነው።

በ2008 ዓ.ም የተጀመረው የመንገድ ፕሮጀክት በ2013 ዓ.ም ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞለታል።

የመንገዱ ግንባታ የሃገሪቱን የወጪ ንግድ ከማሳለጥ ባለፈም ቀጠናዊና አህጉራዊ ትስስርን ለመፍጠር ግብ ላላት አፍሪካ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

በሃይለእየሱስ መኮንን

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.