Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርት ተቋማት መልሶ ግንባታ ዳያስፖራው ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን ጉዳት ያደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባት ዳያስፖራው እገዛ እንዲያደርግ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጥሪውን ያቀረቡት በኢንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በለንደን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች ጋር ባካሄደው ውይይት ላይ ነው፡፡
በውይይቱ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ባደረጉት ንግግር፥ በሁሉም የትምህርት እርከን እየተካሄደ ያለው ማሻሻያ ለመጪው የኢትዮጵያ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ዳያስፖራ ባለሙያዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
አክለውም የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተከሰቱ ግጭቶች የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ለሚደረገው ሀገራዊ ጥረት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ ማቅረባቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.