Fana: At a Speed of Life!

ባለ 500 ተመካካሪ ቡድኖች የቀረቡላቸውን ሃሳቦች እያዳበሩ ይገኛሉ – መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ባለ 500 ተመካካሪ ቡድኖች 250 አባላት ባሏቸው ስልታዊ ቡድኖች የቀረቡላቸውን ሃሳቦች እያዳበሩ ይገኛሉ አሉ የሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)፡፡
ዋና ኮሚሽነሩ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን አሁናዊ ሂደት አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።
ከነሃሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከስምንቱም ቡድኖች በተመረጡ 30 አባላት ከስልታዊ ቡድኖች የቀረቡ የአጀንዳ ምክረ ሃሳቦችን ተቀናጅተው 500 አባላት ላሏቸው 8 የስራ ቡድኖች መቅረብ መጀመራቸውን በመግለጫቸው ላይ ጠቁመዋል።
ይህ የምክክር ደረጃ 500 ተመካካሪዎች በሚወያዩበት አጀንዳ ላይ የመጨረሻ ምክረ ሀሳብ ለማቅረብ ጥልቅ ውይይት የሚያደርጉበት መሆኑን አመልክተዋል።
በእነዚህ የተጠናቀሩ የአጀንዳ ሃሳቦች ላይ የመወያየቱ ሂደት እስከዛሬ ድረስ የቀጠለ ሲሆን፥ 500 አባላት ላሏቸው 8 የስራ ቡድኖች የቀረቡ ሃሳቦችን እያደበሩ ይገኛሉ ነው ያሉት።
በስልታዊ ቡድኖቹ የቀረቡላቸውን አጀንዳዎች አዳብረው የጨረሱ እንዳሉ ጠቁመው፥ ነገር ግን ያላጠናቀቁ ቡድኖች በሚጨርሱበት ጊዜ ቀጣዩ ቡድን እንደሚያስረክቡ ተናግረዋል።
በሶስና አለማየሁ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.