ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማላቦ ከተማ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት ኢኳቶሪያል ጊኒ ርእሰ ከተማ ማላቦ ገብተዋል፡፡
በናይጄሪያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፥ ጉብኝቱን አጠናቀው በአፍሪካ ሕብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ነው ከልዑካን ቡድናቸው ጋር ማላቦ የገቡት፡፡
በቆይታቸውም በሰብዓዊ እርዳታ ፣ ፀረ ሽብር ጉዳዮች ላይ እና ኢ-ሕገመንግሥታዊ በሆነ መንገድ ሥልጣን ለመያዝ የሚደረጉ ጥረቶችን መከላከል ላይ በሚያተኩረው በሕብረቱ ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እንደ ኢቢሲ ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማላቦ ሲደርሱ በአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።